Getachew Melaku Yitbarek
THE SOFT SKILLS CENTER
ኮቺንግ (Coaching) እና ሜንቶሪንግ (Mentoring) ክህሎት ግንባታ
የመሪዎች ዋና ዋና ሚናዎች ሠራተኞችን መምራት፣ አፈጻጸምን ማሻሻል እና የረጅም ጊዜ የሥራ መስክ እድገትን መደገፍ ናቸው።
በሰዋዊ ክህሎት ማዕከል የሚሰጠው ስልጠና ዋና ዋና ይዘቶች
1 የአሰልጣኝነት እና የአማካሪነት መሰረታዊ ነገሮች
· በስልጠና፣ በአሰልጣኝነት እና በአማካሪነት መካከል ያሉ ልዩነቶች እና ተመሳሳይነቶች
· በአጭር ጊዜ የስራ አፈጻጸም ላይ ማተኮር እና በረጅም ጊዜ የስራ ጉዞ ላይ የሚሰጥ መመሪያ/ምክር
· ስነ-ልቦናዊ ደህንነትን እና መተማመንን መፍጠር
· የአሰልጣኙ እና የአማካሪው ሚናዎች፣ ኃላፊነቶች እና የስራ ወሰኖች
2 መሰረታዊ የመግባቢያ ክህሎቶች
· ንቁ የማዳመጥ እና ሁኔታዎችን የመታዘብ ችሎታ
· አሳታፊ እና ሰፊ ምላሽ የሚጠይቁ (open-ended) ጥያቄዎችን የመጠየቅ ችሎታ
· ገንቢ እና በተግባር ሊውሉ የሚችሉ አስተያየቶችን መስጠት
· በሌሎች ቦታ ሆኖ መታዝብ (empathy) እና ስሜታዊ ብልህነትን (emotional intelligence)
3 ማዕቀፎች እና ሞዴሎች
· GROW ሞዴልን (Goal/ግብ፣ Reality/ነባራዊ ሁኔታ፣ Options/አማራጮች፣ Will/ቁርጠኝነት)
· SMART ወይም SPIRIT የተግባር አፈጻጸም ግቦችን ማውጣት
· የተግባር ዕቅዶችን ማዘጋጀት እና የተጠያቂነት አፈጻጸምን መከታተል
4 የፕሮግራም አስተዳደር እና ምርጥ ተሞክሮዎች
· አማካሪዎችን እና ምክር ተቀባዮችን በብቃት ማዛመድ
· አስቸጋሪ ውይይቶችን እና የተለመዱ ተግዳሮቶችን መምራት
· የፕሮግራሙን ስኬት መለካት እና መገምገም


No comments:
Post a Comment