ሢመት በግዕዝ ቋንቋ ሹመት ማለት ነው፡፡ በአንድ አካል መልካም ፈቃድ ለአንድ ግለሰብ ወይም አካል የሚሰጥ ሀላፊነት ነው፡፡ ሹመት ሀላፊነት ብቻም ሳይሆን ተያይዞም ተጠያቂነት ያለበት ነገር ነው፡፡ በመሆኑም ሹመት ሀላፊነትነንና ተጠያቂነት አጣምሮ የያዘ ሲሆን በዚህ ላይ ሀብትንና ስልጣንን በማጎናፀፍ ሀላፊነት የወሰደው አካል አላመውን ማሳካት ይችል ዘንድ የሚሰጥ ፈቃድ ነው፡፡
የሹመት
አንዱና ዋነኛው ባህርይ በሚመለከተው ሰው ወይም በቀጥታ የሚሰጥ ሲሆን ሰጪውም በቀጥታ ተሳትፎ በቃልም በፅሁፍም የሚያፀናው ጉዳይ
ነው፡፡ የሰሞኑ የሀገራችንን የበአለ ሲመት አከባበር የተደበላለቀ ስሜት ፈጥሮ ያለፈ ክስተት ሆኗል፡፡ አንዳንዶች ጉዳዩን ወዲያው
ሲረሱት አንዳንዶች ግን መልዕክቱ ምንድን ነው? ብለው እያብሰለሰሉት ይገኛሉ፡፡
አንዳንዶች
የዚህ አይነት ተግባር ምን ያህል መጀመሪያ ምክንያታዊ ቀጥሎ ህጋዊ ነው? ብለው ሲጠየቁ ይሰማል፡፡ ከህጋዊነት በፊት ምክንያታዊነትን
ያስቀደምኩት አንዳንድ ጊዜ ኢህጋዊ ግን ምክንያታዊ የሆኑ ነገሮች ስለሚገጥሙን ነው፡፡
ወደ
ጉዳዪ ልመለስና ሰሞኑን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት በአለ ሲመት በቃላት ጋጋታ የህብረተሰቡን ሰሜት ለመፈተሽ የተሞከረበት
የሚዲያ ዘመቻንም ያካተተ እንደነበር ብዙዎች ታዝበውታል፡፡ አዲስ መንግስት ምስረታ፣ በአለ ሲመት በመጨረሻም የዶ/ር አብይ በአለ
ሲመት ተብሎ ሲጠራ ቆይቶ፣ በመጨረሻ እንደታየው ጠቅላዩን ባገነነ ሁኔታ ተደምድሟል፡፡
የበአለ
ሲመቱ ዝግጅትና አፈፃፀም ሲታይ ብዙዎች የነገስታትን በተለይ ደግሞ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ተሰንዶ የሚገኘውን የቀ/ኃ/ስን ሲመት እያስታወሱ
ምን ለማለት እንደሆነ ያጠይቃሉ፡፡ በኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም ይሁን በአቶ መለስ ዜናዊ እንሁም በአቶ ሀ/ማርያም ደሳለለኝ ዘመን
ተመሳሳይ አከባበር አላጋጠመኝም፡፡ በመሆኑም የጠ/ሚ አብይ መንግስት ሲመት አንድምታ የአንዳንድ ሰዎችን ቀልብ የሳበ ነበር፡፡ በንጉሱ
ጊዜ ፈጣሪ የሰየመኝ ነኝ የሚልና ተጠያቂነቴም ለእሱ ነው የሚመስል መልዕክት ሲኖረው ህዝቡና መኳንንቱ ለእኔ ተገዥ
(Subject) ነህ የሚል ዕንድምታ አለው፡፡
የጠ/ሚ አብይ ሲመት አከባር እንድምታና መልዕክቱስ?
ጠ/ሚ
አብይ ታዋቂነት (Popularity) የሚያስደስታቸው መሪ እንደሆኑ ለማንም ግልጽ የሆነ ይመስላል፡፡ እንግዲህ የአመራር
ስነእሳቤ እንደሚለው አንድ መሪ በአካለ ቁመናወ ንግግር (Charismatic) ፣ ወይም አምባገነን (Autocratic)፣ ዴሞክራሲዊ
(Democratci) ወይመ ቸልተኛ (Lasses-Fair) ባህርያ አሉት፡፡ የጠሚ አብይ በንግግር፣ በመግባባት በአማላይ ንግግርች
የመጀመሪው ባህርይ የሚያይልባቸው ይመስላል፡፡ ንግግራቸው በይበልጥ አንድነትና፣ ውህደት የሚሰብክና ጠፋ ብለው የሚያስቡት ኢትዮጵያዊ
አንድነትን ለመመለስ እንደሚተጉ ደጋግመው ገልፀዋል፡፡ ይህ በበርካቶች ዘንድ ድጋፍ ቢያስገኝላቸውም አሁንም ይህንን ንግግራቸውን
በጥርጣሬ ከሚያየው እስከ የሚቃወመው ደረስ ተግዳሮት አለባቸው፡፡ ከዚህመ በባሰ ሁኔታ አብዛኞቹ የትህነግ ሰዎች "አሀዳዊ
መንግስት ለመመስረት ይፈልጋለ" ብለው እንደሚከሷቸውም የሚታወቅ ነው፡፡
ከላይ
በሰፈረው ትንታኔ መሰረት ስንመለከት ሲመት ከፈጣሪ ወይም በቀጥታ ምርጫ ከህዝብ ይገኛል ካልን በብዙሃን መገናኛ ብዙ የተነገረለት
በአርኪቴክቶችና ኬያንያን የተደከመለትን ዝግጅት ለምን አስፈለገ? ሲመቱስ መሆነ ያለበት ለጠ/ሚው ነው? እርግጥ ነው ዶ/ር አብይን
የትውልድ መንደራቸው በሻሻ መርጧቸዋል፣ በተነገረውም ውጤት መሰረት የመራጩን 98 ከመቶ ድምፅ አግኝተዋል፡፡ በዚህም የፖለቲካ ስልጣን
ለመያዝ ዝግጅት እያደረጉ እንደነበር የቀደመ መረጃ የሌለው ሰው እንኳን ሊረዳው ይችላል፡፡ ነገር ግን ዶ/ር አብይ በመላው ህዝብ
አልተመረጡም (በአንድ ዝግ ግምገማ "በእኔ ምክንያት ነው ብልጽግና ያሸነፈው" ብለው አቧራ አስነሱ ተብሎ ሀሜት
ቢጤ በከተማው ተነዝቶ ነበር) ደጋፊያቸው ግን በርካታ እንደሆነና ባልተወዳደሩበት ቦታ ሁሉ ብዙ ሰው እሳቸውን ካልመረጥኩ ብሎ ነበር
የሚል ወሬም ተደጋግሞ ተሰምቶ ነበር፡፡ ይህ ስኬት በ Convincing ይሁነ confusing ባይረጋገጥም፡፡ ትንሽ ፈገግ
ለማንኛውም
በእርግጥ በበሻሻ የመመረጣቸው በፓርቲያቸው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የመጠቆማቸው ነገር የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን ጉዳዩ በአለ ሲመታቸውን
ከላይ እንደገለፅነው በአደባባይ ማድረጋቸው ለምን ምክንያት ይሆን? ድርጊቱስ ህጋዊና ምክንታዊ ነውን? ወይስ እንደተባለው ዝግጅቱ
ሲጠናቀቅ ተከሰተ እንደተባለው የግለሰብ ስብዕናን የመገንባት አንዱ ተፍጻሜ ነው? ነገርየው በስዩመ እግዚአብሔር ወይም በቀጥታ በኅዝብ
የተመረጡ ካልሆኑ የዚህ አይነት ሲመት እንደምታው ሌላ ነው ከሚሉት ወገንስ ምን ይሰማል? ሀሳቡን ለማጥራት ያል የተሰነዘረ አስተያየት
ነው፡፡
አውነት
ግን ህገ መንግስቱ የጠሚውም ይሁን የፕሬዚደንቱ በአለ ሲመት በአደባባይ ይከበራል ይላል?
ወጪውንስ
የሚሸፍነው ማን ነው?
ለማንኛውም
መጪውን ለማየት ዋናነው እድሜን መለመን ነው፡፡
No comments:
Post a Comment